Thursday, January 23, 2014

የሰለሙና ወጎች


ጊዜው ህዳር አጋማሽ ነበር - 2013

ረፋዱ ላይ ወደ ከረን የሚወስደውን መንገድ በመተው ወደ ዛግር አቅጣጫ ታጠፍን። ረጅም ጉዞ ስለሚጠብቀን ከወዲ ሓሬና ብዙ ወግ እንደማገኝ ርግጠኛ ነበርኩ። ከሚጠብቁኝ ወጎች መካከል፣ “የስደተኛው ማስታወሻ” ህትመት መቋረጥ፤ የጫልቱ ሚደቅሳ ግለ - ታሪክ ጉዳይ እና የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የግድ የሚነሱ ነበሩ። ሆኖም እንደሚጠበቀው በቀጥታ ወደነዚህ ርእሰ ጉዳዮች አልገባንም። በቅድሚያ ቀላል ወጎችን ተጨዋወትን።

Monday, September 30, 2013

የእሬቻን በአል አከበርኩ!

 ቅዳሜ መስከረም 28, 2013 እዚህ አምስተርዳም ከተማ የእሬቻን በአል አከበርኩ። ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች በአሉን ለማክበር መጥተው ነበር። “ያ! መሬሆ!” እያልን ወደ ውሃው ተጓዝን። ከዚያም ቢጫ አበቦች እና እርጥብ ቅጠል ውሃው ላይ አስቀመጥን። አብዛኛው የበአሉ ታዳሚ የኦሮሞን ባህላዊ ልብስ ለብሶ ነበር። ሴቶች እና ህፃናትም በብዛት ነበሩ። በአካባቢው የነበረ አንድ ሆላንዳዊ በመደነቅ አፉን ከፍቶ ትርኢቱን ይመለከት ነበር።    

Saturday, September 28, 2013

“ላይፍ” መፅሄት - አዲስ አበባ - ቃለመጠይቅ


·         አዲሱየስደተኛው  ማስታወሻመጽሐፍህ የደራሲው  ማስታወሻእና የጋዜጠኛው  ማስታወሻ  በምን  ይለያል? 

Ø  የስደተኛው ማስታወሻ” ከቀዳሚዎቹ ማስታወሻዎች የቀጠለ ነው። በዚህ ቅፅ በተመሳሳይ ገጠመኞቼን ነው ያሰፈርኩት። በርግጥ እንደ ሰንሰለት የተያያዙ የአውሮፓ የስደት ገጠመኞቼ ተተርከውበታል። ይህ ቅፅ የማስታወሻዎቼ መደምደሚያ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ ወደ ስነፅሁፍ ስራዎች ነው የምገባው። 

·         የስደተኛው ማስታወሻአሳታሚ ማነው? መቼ ለገበያ ይቀርባል? 

Ø  ነፃነት አሳታሚይባላል። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የኢትዮጵያውያን ንብረት የሆነ አሳታሚ ድርጅት ነው። ውል አድርገን መፅሃፉን አስረክቤያለሁ። የጀርባና የፊት ሽፋኑን ዲዛይን ሰርተው ልከውልኝ አፅድቄያለሁ። መፅሃፉ በህትመት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነግረውኛል። ጥቅምት ገበያ ላይ ይውል ይሆናል። በትክክል ቀኑን አላውቅም። መረጃዎቹን በድረገፃቸው በኩል ይፋ ያደርጉታል።